ኢሚግረሽን እና ጥገኝነት መጠየቅ  – አስፈላጊ ቃላቶች እና ትርጉማቸው

 

ኢሚግረሽን ኢሚግረሽን ማለት አንድ ሰው ከአንድ አገር ለቆ ወደ ሌላ አገር ውስጥ መኖር ማለት ነው ።

እዚህ አገር UK (ዩ.ከ) ውስጥ በ ኢሚግረሽን ቤት ጽሕፈት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ከ ወደ እዚህ አገር መኖር ለጀመሩ ሰዎች ጋር ይሰራሉ ።

ጥገኝነት ፈላጊ ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ለመኖር ከሀገራቸው ለቀው ወደ ሌላ አገር የስደተኛነት የመኖሪያ ፍቃድ እንዲሰጣአው የሚያመለክቱ ሰው ።
ስድተኛ ወደ አገራቸው መመለሳቸው ደህንነቱ የተጠበቀ አለመሆኑን በማረጋገጣቸው አገራቸውን ጥሎ በሌላ አገር ውስጥ እንዲንሩ የተፈቀዳለው ሰዎች ።
የስደተኞች የመኖሪያ ፍቃድ ሁነኢታ የስድተኛነት ሁኔታ ከትሰጠዎት የአገር ውስጥ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት በዩናይትድ ኪግዶም ውስጥ እንደ ስደተና ሆነው መኖር እንደሚችሉ ፈቅዶሎዎታል ማለት ነው ።
የጥገኝነት ሂደት በ UK (ዩኬ) እንግሊዝ ሃገር ውስጥ የስደተናነት መኖሪያ ፍቃድ ለማግኘት ለማመልከት የሚወስዷቸው እርምጃዎች ።
የዕድሜ ግምገማ ዕድሜዎ ምን ያህል እንደሆነ (ለምሳሌ ፓፕስፖርት ወይም ይልደት ምስከ ወረቀት) እና የአገር ውስጥ ጉዳይ ስሕፈት ቤት ወይም የማህበራዊ ጉዳይ ሠራተኛዎ እርስዎ የሚሉት ዕድሜ ትክከለኛ ነው ብለው ካላመኑ ፣ ዕድሜዎን ለመገመት የሚያደርጉት ምርመራ ነው ።

ይህ ምርመራ ሲካሄድ ፣ ከሁለት የማህበራዊ ሰራተኛ ጋር ስብሰባ ያደርጋሉ ስብሰባው አንዴ ወይም ከአንድ ጊዜ በላይ የሚካሄድ ስብሰባ ሲሆን ብዙ ጥያቄዎች የሚጠየቁበት ስብሰባ ነው ። ይህ ደግሞ እንደሱ ዕድሚዎ ምን ሊሆን ይችላል ብለው ለመገምገም ይሚካሄድ ስብሰባ ነው ።

የእገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስተር ስለ ስደት (ኢሚግረሽን) የሚመልከት ኃላፊነት ያለው የምንግሥት ክፍል ነው ።
ይግባኝ ስለ የኢሚግረኝስ ጉዳይዎ የተሰጦት ውሳኔ እርስዎ ስህተት ነው ብለው ይሚያምኑ ከሆነ ፣ ትክክለኛው ውሳኔ እንዲሰጥዎት ፍርድ ቤት መጠየቅ ይችላሉ ። ይህንን ለማድረግ ጠበቃ / ስለጉዳይዎ የሚከራከርሎት ባለሞያ ይረዳዎታል ።
ፍርድ ቤት በዳኛ የሕግ ውሳኔዎች የሚደረጉበት ቦታ ።
ዋናው ወይም (ትልቅ) ቃለ መጠይቅ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር እርስዎ በአገርዎ ውስጥ ደህነቱ ያልተጠበቀበትን ምክንያቶ የሚጠይቆአት እና በዚህ አገር ውስጥ የስደተኛነት ሁኔታ ይሰጥዎት እንደሆነ የሚወሰነው ትልቅ ቃለ መጠይቅ ነው ።
የሕግ ድጋፍ ለመክፈል በቂ ገንዘብ ለሌላቸው ሰዎች ለጠበቃዎች ለመክፈል ለመንግሥት የሚከፈላቸው አገልግሎት ነው ።

 

ስዎች

የኢሚግረሽ ጠበቃ / የሕግ አማካሪዎች ስለ ሕጉ የሚያውቅ እና የስደተኛነት ሁነታን ከሀገር ውስጥ ጽሕፈት ቤት ለማመልከት ወይም የይግባኝ ውሳኔዎችን ለማግኘት የሚረዳ ሰው ። ወይም የሕግ አማሪዎች ናቸው ።
የጽሑፍ አስተርጓሚr / የቃል አስተጓሚ እርስ በእርስ እንዲግባቡ የተለያዩ ቋንቋዎች የሚናገሩ ሰዎች ፣ አስተርጓሚ ተብለው ይጠራሉ ።
Appropriate Adult በእድሜ ግምገማ ወይም ከሀገር ውስጥ /ቤት ጋር ባደረጉት ትልቅ ቃለ ምልልስ ለራስዎ እንዲናገሩ የሚረዳዎት እና የሚደግዎት ሰው ።
ዳኛ ስለ ጉዳይዎ የሚመልከት ይግባኝ ሲሉ ግዳይዎ ፍርድ ቤት ውስጥ ሲታይ ውሳኔ የሚሰጥ ሰው ።
MP (Member of Parliament) ለአከባቢዎ ወይም ስለ አከባቢ የሚመለከት ኃላፊነት ያለው የመንግስት ፓርላማ አባል የሆነው ሰው ።

ለቃለ መጠይቅዎ ወይም በጉዳዩ ላይ ውሳኔዎን በታም ረጅም ጊዜ ከጠበቁ ፣ የእርስዎ የፓርላማ አባል የሆነ ወደ የአገር ውስጥ ጉዳይ ጽሕፈት ቤት እንዲጽፉ መጠየቅ ይችላሉ ።

እርስዎ በዚህ ሂደት ውስጥ በታም አስፈላጊ የሆኑ ሰው!